ክብርት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የኢ.አ.ፌ ፕሬዝዳንት የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አትሌቶች በመጨረሻው ልምምዳቸው ላይ ተገኝተው አበረታቱ።

የ19ኛውን የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚካፍሉ አትሌቶቻችን ዛሬ የካቲት 18/2016ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከማለዳው 12:30 የመጨረሻውን ልምምዳቸውን አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በቦታው በመገኘት ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን በምክራቸውም የሚከተለውን ብለዋል :-

እኔን ብትመለከቱ ለረጅም ጊዜ ማለትም ወደ ሃያ ሁለት አመት ያክል በአትሌትነት የቆየሁትና የሰለጠንኩት በአሰልጣኝ በዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ነው እናንተም ለረጅም ጊዜ በአንድ አሰልጣኝ መቆየት ለውጤታማነት ይረዳል ሌላው በአንድ ካምፓኒ መቆየት በጣም ጠቃሚ ነው አሰልጣኝ መቀየር ካምፓኒ መቀየር ለእናንተ ውጤታማነት ምንም ጥቅም የለውም ሌላው ምክራቸው አትሌቲክስ ከባድ ነው ተስፋ ያስቆርጣል የአትሌቱ ውጤት በአንድ ጀንበር አይመጣም ግን ከተጋቹ ተስፋ ሳትቆርጡ በዲስፕሊን ከሰራችሁ አትሌቲክስ በጣም ቀላል ነው ሌላው ባላችችሁ እምነት ፀልዩ በርቱ ፤ ከአበረታች ቅመሞች ራሳችሁን ጠብቁ በልፋታችሁ የሰራችሁትን ስታገኙ መልካም ነው ብለዋል ::

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሳትፎና ውድድር ዳይሬክተሩ አቶ አስፋው ዳኜ ተገኝተው አትሌቶች አበረታተዋል ።

መልካም እድል ለውድ አትሌቶቻችን!!

+5

See insights and ads

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *