በግላስጎ በተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ በድል ለተመለሰው ብሔራዊ ቡድናችን አቀባበል ተደረገለት፤

የካቲት 26/2016 ዓ.ም

ከማርች 1-3/2024 በእንግሊዝ ግላስጎ በተካሄደው 19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተካፍሎ በድል ለተመለሰው የልኡካን ቡድን ዛሬ ቀን ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የልዑካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው እና የፌዴሬሽኑ አመራሮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል።

በውድድሩ በ13 አትሌቶች የተወከለችው ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ፣ በአንድ የብር እና በአንድ የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 5ኛ፣ ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ከአቀባበል ስነ ስርዓቱ በኋላ የልኡካን ቡድኑ በክፍት መኪና በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሲዘዋወር ከህዝቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። በመቀጠልም በካፒታል ሆቴል ማርች 25/2024 በቱኒዚያ ሃማማት በተካሄደው አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተካፍሎ ባለፈው ሳምንት ወደ ሃገሩ ከተመለሰው ቡድናች ጋር በጋራ በመሆን በሁለቱም ሻምፒዮና ለተካፈሉ የልኡካን ቡድን አባላት በፌዴሬሽኑ የእውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *