ለፓሪስ ኦሊምፒክ እጩ አትሌቶችና አሰልጣኞች እንዲሁም ለአትሌት ተወካዮች የአለም አቀፉ አትሌቲክስ በ2024 ባወጣው የአበረታች ቅመሞች ህግ ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡

በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ፣ ዶ/ር ተስፋዬ አስግዶም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን የስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር እና የተሳትፎና ውድድር ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ ተገኝተዋል።

በመርሃግብር ማስጀመርያ ላይ ዶ/ር ጊዬን ሰይፈ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክን ቡድን chief demission እና የልኡክ ቡድኑ ሀኪም የሎንግ ሊስት ምዝገባ እንደተካሄደ ፣ከዶፒንግ ጋር በተያያዘ እና አጠቃላይ የህክምና ውሳኔን በተመለከተ ገላጻ አድረዋል ።

ወ/ሪት መልኪቱ ሰጠው የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የምርመራ ክፍል ሃላፊ ስለ የመገኛ አድራሻ ትክክለኛ መረጃ ከመስጠት ጋር እና በመሙላት ደረጃ እንዲሁም በኦሎምፒክ ለመሳተፍ ግዴታ የሆኑ 7 አይነት ምርመራ ማካሄድ ግዴታ በሆኑን አሳስበዋል።

በመቀጠልም ወ/ሮ ቅድስት ታደሰ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የህክምና ከፍተኛ ባለሙያ ስለ አትሌት ባዮሎጂካል ፖስፖርት ምን ያህል ግንዛቤ እንዳላቸው የአንድ አትሌት ለአበረታች ቅሞች ምርመራ የተሰጠ እስከ አስር አመት ናሙና በተጨማሪም ሰፕልመንት/supplement አወሳሰድ ላይ እንዴት ይወሰዳል በሚሉ ጉዳዮች እና የህክምና ምክር ሳያገኙ የሚወሰደውን ሰፕልመንት መጠንንም ጭምር በጥልቀት አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የህክምና ከፍተኛ ባለሙያ ዶ/ር አያሌው ጥላሁንም በአትሌቶች በደም ውስጥ የሚገኝ የሄሞግሎቢን መጠን መዋዠቅ ከአይረን/iron መውሰድ ጋር ተያይዞ የመጣ ስለሚሆን ይህ ደግሞ እንደ አበረታች ቅመም ችግር ስለሚወሰድ አይረን መቼ ይወሰዳል፣ ውድድሩ ምን ያህል ጊዜ ሲቀረው? የሚሉ መሰረታዊ ሀሳብ በማንሳት ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥተዋል ።

ስለ ፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ አጠቃላይ የስልጠና ሂደት፣ የሆቴል ቅድመ ዝግጅት ፣ ቴክኒካል የሆኑ ጉዳዮች ላይ ፣ እንዲሁም ከአትሌቶች አና ከአሰልጣኞ የሚጠበቅ ዲስፕሊን አስመልክቶ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት እንደዚህ አይነት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ስልጠና በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሳሙኤል ብርሃኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን የስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር የተናገሩ ሲሆን

በመጨረሻም በዚህ መርሃ ግብር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮምሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በመድረኩ የመዝጊያ ንግግርራቸው፡-ከቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ትምህርት በመውሰድ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ጠንክሮ መሰራት አንደሚገባ አሳሰበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *