በጋና፣ አክራ ዩንቨርሲቲ ከማርች 18-22/2024 ሲካሄድ የቆየው 13ኛ የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር ፍፃሜውን አገኘ፤

ላለፋት አምስት ቀናት 50 የአፍሪካ ሃገራት ከ640 በላይ አትሌቶች በሁሉም የአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት ሲሳተፋ ሃገራችን ኢትዮጵያ በ47 ወንድ፣ በ40 ሴት በድምሩ በ87 አትሌቶች ተወክላ ስትሳተፍ በሜዳልያ ሰንጠረዝ ውስጥ መግባት ከቻሉት 27 ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ በ7ወርቅ፣ በ7 ብር እና በ4ነሀስ በድምሩ በ18 ሜዳልያዎች ናይጄሪያን ተከትለን 2ኛ ደረጃ ይዘን አጠናቀናል።

በዛሬ እለት ፍፃሜ ያገኙ ውድድሮች፦

በከፍታ ዝላይ ወንዶች፦

11ኛ ዱፕ ሊም በ2.10 ሜትር

በርዝመት ዝላይ ወንዶች፦

8ኛ ቡሊ መላኩ በ7.61 ሜትር

በወንዶች ጦር ውርወራ፦

7ኛ ኡታጌ ኡጉላ በ73.84 ሜትር

8ኛ ኦክት ጀምስ በ69.61 ሜትር

12ኛ ኦታዋ ኦኬሎ በ62.42 ሜትር

400ሜትር መሠናክል ሴቶች፦

6ኛ ትዕግስት አያና በ59.89

አሎሎ ውርወራ ሴቶች

7ኛ ዙርጋ ኡስማን በ13.92 ሜትር

10ኛ አይናለም ነጋሽ በ11.09 ሜትር

በግማሽ ማራቶን ሴቶች ፍፃሜ፦

🥈ዘውዲቱ አደራው በ1:14:40 🇪🇹

6ኛ አታለል አንሙት በ1:16:28

አዲሴ ምስለኔ አቋርጣለች

በግማሽ ማራቶን ወንዶች ፍፃሜ፦

5ኛ ሀፍታሙ አባዲ በ1:06:13

ተሰማ መኮንን አቋርጧል

ማስረሻ ብሪ አቋርጧል

በ5000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ

🥇ሀጎስ ገ/ሕይወት በ13:38.12🇪🇹

4ኛ ኩማ ግርማ በ13:43.58

5ኛ ጌትነት ዋለ በ13:44.45

በ1500 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ

🥇ሂሩት መሸሻ በ4:05.71 🇪🇹

🥈ሃዊ አበራ በ4:06.09🇪🇹

4ኛ ቢቂሌ አንበሱ በ4:07.67

በ1500 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ

🥈ኤርሚያስ ግርማ በ3:39.40 🇪🇹

4ኛ ወገኔ አዲሱ በ3:39.54

10ኛ ዘነበ በላቸው በ3:43.85

በ4X400 ሪሌ ሴቶች

4ኛ ደረጃ ኢትዮጽያ በ3:42.77

በ4X400 ሪሌ ወንዶች

8ኛ ደረጃ ኢትዮጵያ በ3:29.77 በሆነ ሰዓት አጠናቀናል።

እንኳን ደስ አለን!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *