በ13ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ዛሬ መጋቢት16/2016 ዓ.ም ምሽት 3:30 አዲስ አበባ ገብቷል።

በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ስምንተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑክ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።

የመላ አፍሪካ ጨዋታ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 / 2016 ዓ.ም በጋና-አክራ ኢትዮጵያ በ9 የስፖርት አይነቶች ተሳትፋለች።

ኢትዮጵያ በ9 ወርቅ፣ 8 ብር እና 5 ነሐስ በአጠቃላይ 22 ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሁሉም የስፖርት አይነቶች ስምንተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች ሲሆን በአትሌቲክሱ 7 ወርቅ፣ 7 ብር እና 4 ነሐስ ሜዳሊያዎች በማግኘት በ2ኛ ደረጃ አጠናቃለች።

ልዑኳኑ ቡድን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤናና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ ፣በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተቀ/ምክ ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፣ አቶ ተፈራ ሞላ (አቃቢ ንዋይ) እና በረ/ኮምሽነር አትሌት ማርቆስ ገነቴ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹