በ45ኛው ዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የሁለተኛነት ደረጃ በመያዝ ጨርሳለች፡፡

*****************************************************

መጋቢት 21/2016 ዓ.ም

ማርች 30/2024 በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው የ45ኛው ዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአምስት ምድቦች ማለትም 8ኪ.ሜ. ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ፣ 6 ኪ.ሜ. ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ፣ 4×2 ኪ.ሜ የድብልቅ ሪሌ ሴት/ወንድ ፣ የ10 ኪ.ሜ. የአዋቂ ሴቶች እና አዋቂ ወንዶች በተካተቱበት ውድድር ከ51 አገራት የመጡ 485 የሚሆኑ አትሌቶች ተፎካክረውበታል። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያ በ14 ሴት እና በ14 ወንድ በ28 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን በ ሁለት ወርቅ ፣በስድስት ብር እና በሁለት ነሃስ በአጠቃላይ በ10 ሜዳሊያ ከአለም የሁለተኛነት ደረጃ በመያዝ ውድድሩርን ጨርሳለች ፡፡

🇪🇹 እንኳን ደስ አለን!

#WorldCrossCountry

#wabelgrade24