በ45ኛው የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሀገራችንን ወክሎ የተሳተፈው የልዑካን ቡድናችን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም ደርሷል ።

⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳⨳

መጋቢት 24/2016 ዓ.ም

የልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው ፣ የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የቴክኒክና የሕዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ፣ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የቢሮ ሃላፊዎች ፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

በተጨማሪ የእንኳን ደህና መጣችሁ የአበባ ጉንጉን መርሃግብር ተደርጓል ።

የኢትዮጵያ አትሌቶች ደጋፊዎች ማህበር ማርሽ ባንድ የደመቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

🔷ጀግኖች አትሌቶቻችንና የልዑካን ቡድን አባላት እንኳን በድል ተመለሳችሁ!