የኢትዮጵያ የአጭር መካከለኛ፣ 3000 ሜ መሠ.፣ የሜዳ ተግባራትና የእርምጃ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የበላይነት ተጠናቀቀ።

ለአምስት ተከታታይ ቀናት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲካሄድ የሰነበተው የኢትዮጵያ የአጭር መካከለኛ፣ 3000 ሜ መሠ.፣ የሜዳ ተግባራትና የእርምጃ ውድድር ላይ 20 ክለቦችና ተቋማት 460 ወንድ ፣ 319 ሴት በድምሩ 779 አትሌቶች የተወዳደሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ በሴት፣ በወንድ እንዲሁም በአጠቃላይ በ361 ነጥብ 1ኛ በመውጣት የሶስት ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊዎች:-

🔷በሴቶች አሸናፊ

በ191.5 1ኛ ኢትዮጵያ ንግድባንክ 🏆

በ 164 2ኛ መቻል

በ 87.5 3ኛ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ

🔷በወንዶች አጠቃላይ አሸናፊ

በ169.5 1ኛ ኢትዮጵያ ንግድባንክ🏆

በ134 2ኛ መቻል

በ125.5 3ኛ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ

🔷 አጠቃላይ በወንድ እና በሴት አሸናፊ

በ361 1ኛ ኢትዮጵያ ንግድባንክ 🏆

በ298 2ኛ መቻል

በ213 3ኛ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ

በአምስተኛ ቀን የተከናወኑ የፍፃሜ ውድድሮች ውጤት፦

🔷1500 ሜትር በሴት

1ኛ ሂሩት መሸሻ ከኢት/ኤሌክትሪክ 4:10.07

2ኛ ትዕግስት ግርማ ከመቻል 4:11.55

3ኛ ሕይወት መሃሪ ከኢት/ንግድ ባንክ 4:12.74

🔷1500 ሜትር በወንድ

1ኛ አድሃና ካሳይ ከኢት/ንግድ ባንክ 3:41.76

2ኛ ሣሙኤል አባተ ከመቻል 3:42.22

3ኛ ዮሐንስ አስማረ ከኢት/ኤሌክትሪክ 3:42.60

🔷4×100 ሜትር ዱላ ቅብብል በሴት

1ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ 47.32

2ኛ መቻል 47.94

3ኛ ኢት/ንግድ ባንክ 48.20

🔷4×100 ሜትር ዱላ ቅብብል በወንድ

1ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ 41.37

2ኛ መቻል 41.44

3ኛ ኢት/ ንግድ ባንክ 41.72

🔷4×400 ሜትር ዱላ ቅብብል በወንድ/ሴት

1ኛ ኢት/ ንግድ ባንክ 3:24.66

2ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ 3:25.90

3ኛ መቻል 3:28.01

🔷4×800 ሜትር ዱላ ቅብብል በወንድ/ሴት

1ኛ ሸገር ሲቲ 7:52.37

2ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ 7:55.00

3ኛ ኦሮ/ኮን/ኢንጂነሪንግ 7:57.26

🔷ምርኩዝ ዝላይ በወንድ

1ኛ አበራ አለሙ ከጥሩነሽ ዲባባ 3.75 ሜትር

2ኛ ቴዎድሮስ ሽፈራው ከመቻል 3.60 ሜትር

3ኛ ሳምሶን በሻ ከሸገር ሲቲ 3.60 ሜትር

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ምክ/ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክ/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የኢትዮ ቴሌኮም የካምፔን አና ኢቬንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ሰኚወርቅ ለማ፣ የኤክሴል ማርኬቲንግና ኮንሰልቲንግ ስራ አስኪያጅ አቶ ሮቤል ሰይዶ ፣ የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የቴክኒክና የህዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ ፣ የኢ.አ.ፌ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ የኢ.አ.ፌ ማኔጅመንት አባላት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ደጋፊዎች ማህበር በውድድሩ ላይ ተገኝተዋል ።

ውድድሩን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ደጋፊዎች ማህበር ማርሽ ባንድ በመክፈቻ እና በመዝጊያ ላይ በመገኘት ውድድሩን አድምቀውታል ።

ምስጋና

👉ለፕላቲንየም ስፖንሰራችን ኢትዮ ቴሌኮም

👉ለብራንድ ስፖንሰራችን አዲዳስ ካምፓኒ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *