የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በጋራ በመሆን ለሃገር ባለውለታና አንጋፋ አትሌቶች የገና በዓል ስጦታ አበረከቱ ፤

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በጋራ በመሆን በኦሎምፒክ ኮሚቴ ግቢ ባዘጋጁት መርሀግብር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸጘ አበራ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አቃቤ ንዋይ ዶ/ር ኤደን አሽናፊ እና አቶ ቢልልኝ መቆያ የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ቴክኒክ እና ሕዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ ተገኝተዋል።

በዚህ መርኃግብር ላይ ለ124 የሃገር ባለውለታ ለሆኑ አንጋፋ አትሌቶች የበዓል መዋያ ገንዘብና የአትሌቲክስ ሙሉ ስፖርት ትጥቅ ስጦታ ከረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ ከዶ/ር ኤደን አሸናፊ፣ ከአትሌት ገዛኝኸ አበራ እና ከኮማንደር አትሌት ጌጤ ዋሚ እጅ የተረከቡ ሲሆን ለእያንዳንዱ አንጋፋ አትሌት ‌ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺ ብር) እንዲሁም ‌ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሙሉ የብሔራዊ ቡድን የስፖርት ትጥቅ የተበረከተላቸው ሲሆን ለተደረገላቸው ስጦታ የሃገር ባለውለታዎቹ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *