41ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡

ጥር 5/2016 ዓ.ም

#########################⨳#

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየአመቱ ከሚያከናውናቸው ውድድሮች አንዱ በጥር 5/2016 ዓ.ም በጃንሜዳ ለ41ኛ ጊዜ የሚካሄደው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና አንዱ ነው ፡፡

የውድድሩ ዓላማም፡-

👉 ክልሎችን፣ ከተማ አስተዳድሮችን፣ ክለቦችና የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከላት አትሌቶች በኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር የመሳተፍ ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ፣

👉 እ.ኤ.አ ፌብሯሪ 25/2024 በቱኒዚያ ቱኒዝ ከተማ ለሚካሄደው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና እንዲሁም እ.ኤ.አ ማርች 30/2024 በቤልግሬድ ሰርቢያ ከተማ ለሚካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮዽያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ እና

👉በዉድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታታት ሲሆን

የውድድሩም አይነት

🔷በሴቶች በ6ኪ.ሜ ወጣት እና በ10ኪ.ሜ አዋቂ

🔷በወንዶች በ8 ኪ.ሜ ወጣት እና በ10ኪ.ሜ አዋቂ እንዲሁም በድብልቅ ሪሌ በ8 ኪ. ሜ ነው::

ከዉጭ አገር የሚሳተፉ ከኬኒያ ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ሲሆኑ ከሶስቱ አገራት ከእያንዳዳቸው ሁለት ሁለት አትሌትቶች በአጠቃላይ ስድስት አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡

ከአገር ውስጥ አምስት ክልሎች፣ አንድ ከተማ አስተዳደር፣ ሃያአምስት ክለቦችና ተቋማት እና ቬትራን እና በርካታ የግል ተወዳዳሪዎች ሲሆኑ በወንድ 646 በሴት 331 በአጠቃላይ 977 አትሌቶች ይካፈላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

👉በሁሉም ምድብ ከ1ኛ – 3ኛ ለሚወጡ አትሌቶች የወርቅ፣ የብር እና የነሐስ ሜዳልያ ይሸለማሉ።

👉በውድድሩ ከ1ኛ – 6ኛ ለሚወጡ አትሌቶች በሁሉም የውድድር ምድቦች እንደየ ደረጃቸው የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል።

ውድድሩ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።

See insights and ads

Boost post

All reactions:

132132

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *