53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፤

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓመቱ በሃገር ውስጥ ለማካሄድ ካቀዳቸው ውድድሮች መካከል አንጋፋውና በርካታ አትሌቶችን ያፈራውን ዘንድሮ ለ53ኛ ጊዜ ከጥር 21-26/2016 በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮናን አስመልክቶ በዛሬው እለት በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳና የተሳትፎና ውድድር ዳይሬክተሩ አቶ አስፋው ዳኜ በጋራ ሰጥተዋል።

በጋዜጣዊ መግለጫም የሻምፒዮናው ዋና አላማ፡-

👉🏾 እ.ኤ.አ ከጁን 19-23/2024 በካሜሮን ያሁንዴ ለሚካሄደው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ፤

በጋዜጣዊ መግለጫውም የሻምፒዮናው ዋና አላማው ፡-

👉🏾 እ.ኤ.አ ከጁን 19-23/2024 በካሜሮን ያሁንዴ ለሚካሄደው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ፤

👉🏾 እ.ኤ.አ ከማርች 8-23/2024 በጋና አክራ ለሚካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና አትሌቶችን መምረጥ፤

👉🏾 እ.ኤ.አ ከጁላይ 26 እስከ ኦገስት 11/2024 በፈረንሳይ ፖሪስ ለሚካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች አትሌቶች ብቃታቸውን እንዲለኩበት

👉🏾 በክልሎች፣ በከተማ አስተዳድሮች፣ በክለቦችና በማሠልጠኛ ማዕከላት ለሚገኙ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም

👉🏾 ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፤ ታስቦ መዘጋጀቱ ተገልፃል።

በውድድሩ ላይ ከ1100 በላይ አትሌቶች ክልላቸውን፣ ክለባቸውንና ተቋማቸውን ወክለው የሚሳተፉ ሲሆን ለአሸናፊ አትሌቶችም ከ540 ሺ ብር በላይ ለሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን ከዚህ ቀደም ሃገር የወከሉ ታዋቂ አትሌቶችም የሚሳተፋ ይሆናል።

ለውድድሩ ፌዴሬሽኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰለጠኑ ዳኞችን እና የውድድር አመራሮች እንዲሁም አስፈላጊውን በጀት መመደቡ የተገለፀ ሲሆን የመክፈቻና የመዝጊያ ቀን በቀጥታ ስርጭት በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል ለአትሌቲክስ ወዳዱ ማህበረሰብ በቴሌቪዥን የሚተላለፍ መሆኑንም ጭምር በመግለጫው የተገለፀ ሲሆን ፌዴሬሽኑ በመጨረሻም የፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰርና የሁልግዜምአጋር ለሆነው ኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም ለብራንድ ስፖንሰሩ ለአዲዳስ ኩባንያ ምስጋና አቅርቧል።

See insights and ads

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *