53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ጥር 21/2016 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ1963 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኝ ሻምፒዮና ሲሆን ዘንድሮ ለ53ተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከጥር 21-26/2016 ዓ.ም ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ይከናወናል ።

👉 በጠዋቱ መርሃግብር በ1ኛ ቀን ፍፃሜ ያገኙት ውድድሮች:-

🔷በርዝመት ዝላይ ሴቶች

1ኛ ፖች ኡመድ ከኢት/ንግድ ባንክ 5.86

2ኛ በፀሎት አለማየሁ ከመቻል 5.81

3ኛ አስቴር ቶሎሣ ከሸገር ሲቲ 5.77

🔷በከፍታ ዝላይ ወንዶች

1ኛ ዶል ማች ከኢት/ንግድ ባንክ 2.06

2ኛ ዶኘ ሌም ከሲዳማ ቡና 2.03

3ኛ ማል ጐኝ ከኢት/ኤሌትሪክ 2.03

👉ሻምፒዮናውንም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ይፋዊ የመክፈቻ ፕሮግራም በእለቱ የክብር እንግዳ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ክቡር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በዚህ ውድድር ላይ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ምክ/ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊ አቶ ዳዊት አስፋው፣ ታዋቂ አትሌቶችና አሰልጣኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በውድድሩ ላይ ተገኝተዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *