53ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ የበላይነት ተጠናቀቀ ፤

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አንጋፋውና በርካታ አትሌቶችን ያፈራውን ዘንድሮ ለ53ኛ ጊዜ ከጥር 21-26/2016 በአዲስ አበባ ከተማ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተካሄደው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ1100 በላይ አትሌቶች ክልላቸውን፣ ክለባቸውንና ተቋማቸውን ወክለው የተሳተፋበት እና ጠንካራ ፉክክር የታየበት ሻምፒዮና ሆኖ ተጠናቋል። በዚህ ሻምፒዮና በሴትም በወንድም በአጠቃላይ በወንዶች እና በሴቶች በ360 ነጥብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊና የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን በ253 ነጥብ ሁለተኛ መቻል ፣ በ216 ኢት/ኤሌክትሪክ ክለብ ሦስተኛ ደረጃን በመይዝ አጠናቀዋል ።

👉በ6ኛው እና በመጨረሻው ቀን የተካሄዱ የፍፃሜ ውድደሮች ውጤት:-

🔷በምርኩዝ ዝላይ ሴት

1ኛ ጫልቱ ኢተፋ ከኢት/ስፖ/አካዳሚ 2.75

2ኛ አርያት ኦባንግ ከጥሩነሽ ዲባባ 2.6

🔷በ4×400ሜ. ሪሌ ወንድ

1ኛ መቻል በ3፡11.20

2ኛ ሲዳማ ቡና በ3፡11.45

3ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ በ3፡12.44

🔷በ10,000 ሜትር ወንድ

1ኛ ቦኪ ዲሪባ ከሸገር ሲቲ 28፡30.23

2ኛ ንብረት መላክ ከአማራ ክልል 28፡30.65

3ኛ ገመቹ ዲዳ ከኢት/ኤሌክትሪክ 28፡30.67

🔷በ4×400ሜ. ሪሌ ሴት

1ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ በ3፡42.40

2ኛ ሸገር ሲቲ በ3፡43.46

3ኛ መቻል በ3፡46.53

🔷 በ4×100ሜ. ወንድ

1ኛ ኢት/ንግድ ባንክ በ41.20

2ኛ ኦሮ/ክልል በ41.35

3ኛ መቻል በ41.61

🔷በ4×100ሜ. ሪሌ ሴት

1ኛ መቻል በ46.53

2ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ በ46.56

3ኛ ኢት/ንግድ ባንክ በ47.24

🔷በ1500 ሜትር ወንድ

1ኛ ኤርሚያስ ግርማ ከሲዳማ ቡና 3፡42.27

2ኛ ወገኔ አዲሱ ከሲዳማ ክልል 3፡43.37

3ኛ ዘነበ በላቸው ከኦሮ/ክልል 3፡44.44

🔷በ1500 ሜትር ሴት

1ኛ ሃዊ አበራ ከኦሮ/ክልል 4፡07.68

2ኛ ብቅሌ አምበስ ከኦሮ/ፖሊስ 4፡09.29

3ኛ ሳምራዊት ሙሉጌታ ከመቻል 4፡09.61

🔷በ5000 ሜ. 2፡30 ሴት

1ኛ ብርቱኳ ሞላ ከኢት/ኤሌክትሪክ 15፡54.31

2ኛ የኔዋ ንብረት ከኢት/ንግድ ባንክ 15፡54.82

3ኛ አሳየች አይቸው ከኢት/ንግድ ባንክ 15፡56.05

በሴቶች አጠቃላይ አሸናፊ

በ208 ነጥብ 1ኛ ኢት/ንግድ ባንክ 🏆

በ151 ነጥብ 2ኛ መቻል

በ87 ነጥብ 3ኛ ኢት/ ኤሌክትሪክ

በወንድ አጠቃላይ አሸናፊ

በ152 ነጥብ 1ኛ ኢት/ንግድ ባንክ 🏆

በ129 ነጥብ 2ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ

በ102 ነጥብ 3ኛ መቻል

አጠቃላይ በወንድ እና በሴት አሸናፊዎች

በ360 ነጥብ 1ኛ ኢት/ንግድ ባንክ 🏆

በ253 ነጥብ 2ኛ መቻል

በ216 ነጥብ 3ኛ ኢት/ኤሌክትሪክ

👉በሻምፒዮናው ማብቂያ ላይ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እና በእለቱ የክብር እንግዳ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት

የመዝጊያ ንግግር የተደረገ ሲሆን

በዚህ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቀ/ምክ/ፕሬዝዳንት ኮ/ር አትሌት ብርሃኔ አደሬ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀ/ምክ/ፕሬዝዳንት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮም ቺፍ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መሳይ ውብሸት እንዲሁም የስፖንሰርሺፕ እና ኢቬንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ ሰኚወርቅ ለማ፣ የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የቴክኒክና የሕዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች/ኮሚሽነሮች የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንቶች፣ ታዋቂ አትሌቶችና አሰልጣኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ደጋፊዎች ማህበር በመዝግጊያ መርሃግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

❇️የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ደጋፊዎች ማህበር በማርሽ ባንድ የመዝጊያ መርሀ-ግብሩን በማጀብ አድምቀውታል

ምስጋና፦

👉የፕላቲንየም ስፖንሰር ኢትዮ ቴሌኮም

👉ብራንድ ስፖንሰር አዲዳስ ካምፓኒ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *