የጃፓን የካሳማ ከተማ ከንቲባ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረጉ ።

ጥር 30/2016 ዓ.ም

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በጃፓን አገር ካሳማ ከተማ ላለፋት ተከታታይ አምስት አመታት በዲሴምበር ወር በጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ ለመዘከር የግማሽ ማራቶን ውድድር የሚዘጋጅ ሲሆን የውድድሩ አዘጋጅ የካሳማ

ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ ዛሬ 30/05/2016 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ አይነት ያላቸው የስፖርት ትጥቅ ድጋፎችን አስረክበዋል።

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የካሳማ ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ ለአትሌቶች ለስልጠና የሚሆናቸውን ትጥቆች በማምጣታቸው ደስ መሰኘታቸውን የገለፁ ሲሆን ትጥቆቹ የተሰበሰቡት በ2023 በካሳማ በተካሄደው የአበበ በቂላ መታሰቢያ ውድድር ላይ ከተሳተፋ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በየዓመቱ ድጋፉ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በመቀጠል የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ስለድጋፋ አመስግነው ቀጥሎ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በበኩላቸው ለተደረገውን ድጋፍ በፌዴሬሽኑ ስም በማስገን ፌዴሬሽኑ ላሉት የአትሌቲክስ ፕሮጀክቶች እንደሚያደርሱ ገልጸዋል ፡፡

በጃፖን የኢትዮጵያን አምባሳደር አምባሳደር ዳባ ደበሌ ባደረጉት ንግግር ጃፓን እና ኢትዮጵያ ወደ መቶ አመት የሚጠጋ ግኑኝነት ያላቸው ሲሆኑ ከጃፓን ለተደረገው ድጋፍ የካሳማ ከቲባን አመስግነው ኢትዮጵያን በአበበ በቂላ ለማስተዋወቅ ስለሚሰሩት የስፖርት ዲፖሎማሲ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን አመስግነዋል ።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ፣ የኢትዮጵያን ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳን ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣ የካሳማ ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ ተገኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *