በቱንዚያ ቱኒዝ ለሚደረገው ለ6ኛው የአፍሪካ የአገር አቋራጭ ውድድር ዝግጅቱ ተጀምሯል ።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ለአራት አመታት ተቋርጦ የነበረው እና በConfederation of Africam Athletics (CAA) የሚዘጋጀው የአፍሪካ የአገር አቋራጭ ውድድር ዘንድሮ ለ6ኛ ጊዜ በቱኒዚያ ፌብሩዋሪ 25/2024 ይካሄዳል ለዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቻችን አሰልጣኞችን የህክምና ባለሙያዎችን በመምረጥ ከማክሰኞ የካቲት 8/2016 ዓ.ም ጀምሮ በለገጣፎ ለገዳዲ በሚገኘው ስለሺ ስህን ሆቴል በማስገባት ልምምዳቸውን እንዲጀምሩ አድርጓል ።

በዚህ ውድድር ላይ የሚኖሩ የውድድር ተግባራት ከ20 ዓመት በታች በሴቶች 6ኪሜ እና በወንዶች 8ኪሜ፣ በአዋቂዎች 10ኪ.ሜትር ወንድና ሴት እንዲሁም ድብልቅ ሪሌ ናቸው።

በሻምፒዮናው ሃገራችን ኢትዮጵያ በ14 ሴቶች በ14 ወንዶች በአጠቃላይ በ28 አትሌቶች ትወከላለች ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *