በዛሬው የሽኝት መርሃ ግብር የ19ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና የ6ኛው የአፍሪካ የአገር አቋራጭ ሻምፒዮና የልዑካን ቡድን የተሸኙ ሲሆን :-

በሽኝት መርሃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል ” ሁላችሁም በመተጋገዝ፣ ለጋራ ድል በአንድነት ሃገርችንን የምትወክሉ አትሌቶቻችን የምንወዳትን የአገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም አደባባይ በማውለብለብ የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ በማለት በመጨረሻም አጋሮቻችንን አዲዳስ ካምፓኒ፣ ኢትዮ ቴሌኮምንና ኦሮሚያ ባንክን አብረውን ከፌዴሬሽኑ ጋር ስለሚሰሩ ምስጋናዬን በራሴና በፌዴሬሽኑ ስም አቀርባለሁ” በማለት መልእክት ያስተላፉ ሲሆን

የእለቱ የክብር እንግዳ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ለአትሌቶች እና ለልዑካኑ የመልካም ምኞት መግለጫ እና የስራ መመሪያ ሰጥተዋል ።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ አቃቤ ነዋይ ክብርት ዶ/ር ኤደን አሸናፊ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቶች ፣ የፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ የቴክኒክና የሕዝብ ግንኙነት ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ እንግዳ፣ በመርሃግብር ላይ ተገኝተዋል ።

አትሌት ገመቹ ዲዳ እና ጉዳፍ ፀጋዬ የነበራቸው ዝግጅት መልካም እንደነበር እና በጥሩ አቋም ላይ እንዳሉ በመግለፅ ከአምናው የተሻለ ጥሩ ውጤት ለማምጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል ።

የልዑካን ቡድኑን አሰልጣኞች ረ/ኮሚሽነር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ እና አሰልጣኝ ህሉፍ ይህደጎ ስለነበራቸው ስልጠና ልምምድ መልካም እንደነበር በማንሳት ከፈጣሪ ጋር በቀጣይ በሚኖረን ውድድር ጥሩ ውጤት እንደሚያመጡ ተናግረዋል ።

👉ዛሬ ከሌሊቲ 7:00 የ6ኛው የአፍሪካ የአገር አቋራጭ ልዑካን ቡድን ወደ ቱኒዝያ ያቀናል።

መልካም እድል ለውድ አትሌቶቻችን !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *