በ6ኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሁለተኝነት የሚዳሊያ ሰንጠረዥ በመያዝ አጠናቃለች

👉በዛሬው እለት የካቲት 17/2016 በቱኒዝያ ሃማመት በተደረገው 6ኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትያጵያን ጨምሮ አስራ አንድ ሃገራት የተካፈሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ወጣት ሴት 6 ኪ.ሜ.፣ በወጣት ወንድ 8 ኪ.ሜ.፣ በአዋቂ ሴትና ወንድ 10 ኪ.ሜ እና በድብልቅ ሪሌ በአጠቃላይ በ28 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን

በግል እና በቡድን ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብር እና ሦስት ነሃስ በድምሩ አሥር ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአፍሪካ ከኬንያን በመከተል የሁለተኝነት ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

🇪🇹እንኳን ደስ አለን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *